መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከሚያስተምሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር ግምታቸው 120 ሚሊዮን ብር የሚገመት 15,000 የተለያዩ መጻሕፍት በድጋፍ አስገፕ::
መጻሕፍቱም በዋናነት የኢንጂነሪንግ ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ፣ የአካውንቲንግ፣ የኢኮኖሚክስ፣ የማርኬቲንግ፣ የሰው ሃብት አስተዳደር፣ የቋንቋና ሥነልሣን ፣ የሥነፅሁፍ፣ ጂኦግራፊ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢኮኖሜትሪክስ፣ ፊዚክስ፣ ኢኮሎጂ፣ ሂሳብ እና የመሳሰሉት ሲሆኑ ከከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጀምሮ እስከዩኒቨርስቲ ደረጃ ለመማሪያ እና ለማጣቀሻነት (reference) የሚያገለግሉ ናቸው::
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲም እነዚህን በውጭ ከሚገኙ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች የተበረከቱለትን መጻሕፍት ከድጋፍ አድራጊዎቹ ጋር በመመካከር ለሌሎች ተቋማትም ድጋፍ ለግሷል::
በዚሁ መሠረት ዩኒቨርሲቲው በድጋፍ ካገፕው 15,000 መጻሕፍት ውስጥ በጦርነት ለተጎዱት ወሎ (4,000) እና ወልድያ (4,000) ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም 3,000 መፅሐፍትን ደግሞ ለአብርሆት ቤተመጻሕፍት አበርክቷል::
እነዚህን መጻሕፍት በመግዛትና ወደ አገር ቤት በማስመጣት ሂደት በገንዘብና ጊዜያቸውን በመሰዋት ከፍተኛውን ሚና የወጡት በአረብ ኤምሬቶች የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚያስተምሩት እነ ዶ/ር አብዱልወሃብ አደም ኢብራሂም ፣ ዶ/ር አብዮት ምንዳዬ ተሰማ ፣ ዶ/ር እዮብ ጥላሁን መንግስቴ ፣ መ/ር አብዱረዛቅ ከዲር ሀምዛ ፣ እንዲሁም ዶ/ር ጫንያለው ታዬ ናችው:: በተጨማሪም ለዚህ ድጋፍ እውን መሆን በአቡዳቢ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ኮሙኒቲ አባላት ድጋፍም ከፍተኛ ነበር::
የመጻሕፍት ርክክቡ ስነስርዓትም የትምህርት ሚኒስቴሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ዲኤታ ወ/ሮ ብርቱኳን አያኖ እንዲሁም የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር በዛብህ ወንድሙ በተገኙበት በአብርሆት ቤተመጻሕፍት ተካሄዷል:: በተጨማሪም የወሎና ወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች የአብርሆት ቤተመጻሕፍት ዋና አስተባባሪ ፣ የኢትዮጵያና የኦሮሚያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ኃላፊዎች ተገኝተዋል::